አመሰራረት


የአዲስ አበባ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 341/1995 መሠረት በ1997 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከ4000 በላይ አባላት አሉት፡፡.


ርዕይ


በ2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ውስጥ በራሱ ዓቅም የሚንቀሳቀስ ጠንካራ ፣ ታዋቂ ፣ የአምራቹን ውክልና የያዘ ተወዳዳሪ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት መሆን


ተልዕኮ


በማምረት ዘርፍ ለተሠማሩ አባላቱ ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን በጊዜው በመስጠት፣ ምሳሌነት ያላቸው የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ምርጥ የአሠራር ዘዴዎችን በመጠቀም አምራች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንዲስፋፉ ማድረግ ነው፡፡


ዋና ዋና ተግባራትና የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የወረዳ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችን ተግባራት ማስተባበር፤
  • አምራቾች በሥራ ሂደታቸው የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እያጠኑ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የመፍትሔ ሃሳብ ማቅረብ፤
  • የአባላቱን መዋጮ መወሰን፤
  • ለሚሰጡ አገልግሎቶች ዋጋ ማስከፈል፤
  • ለአባላት የተለያዩ ሥልጠናዎች መስጠት፤
  • አምራቾች በጋራ የማምረት እና የግብይት አቅማቸውን ለማሳደግ በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ላይ መምከር እና መተግበር፤
  • የሚመለከተውን አካል በማስፈቀድ በሀገር ውስጥ ወይም በውጭ ሀገር የምርት ትርዒት ማዘጋጀት ወይም መሳተፍ፤
  • በንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከል አለመግባባትና ክርክር ሲፈጠርና ባለጉዳዮች ሲጠይቁ በግልግል አይቶ መወሰን፤
  • የምርት ጋዜጣ፣ መጽሔት እና ሪፖርት ማዘጋጀት፣ የቴክኖሎጂና የገበያ መረጃዎችን ለአባላት ማሰራጨት፤
  • የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ለአባላት ማሳወቅ መንግስት በሚያዘጋጃቸው የውይይት መድረኮች መሳተፍ

የዘርፍ ምክር ቤቱ አባላት

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የ10ሩም ክ/ከተማ ዘርፍ የማኅበራት ምክር ቤቶች እና በከተማ ደረጃ በቀጥታ የሚደራጁ የዘርፍ ማኅበራት የቀጥታ አባላት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የየክ/ ከተማ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘርፍ ማኅበራት አባላት አሉት፡፡

  1. የቤት እንስሳት አርቢዎች እና የእንስሳት ተዋፅኦ አምራቾች ማኅበር፤
  2. የልብስ እና የሸራ ሰፊዎች ማኅበር፤
  3. የጋራዥ ማኅበር
  4. የእህል ወፍጮ ባለንብረቶች ማኅበር
  5. የባልትና እና የባህላዊ ምግብ ውጤቶች አምራቾች ማኅበር
  6. የጌጣጌጥ እና የባህላዊ ዕቃዎች አምራቾች ማኅበር
  7. የብረታ ብረት ውጤቶች አምራቾችና አንጥረኞች ማኅበር
  8. የሸክላ ስራ አምራቾች ማኅበር
  9. የሲልክ ፣ ስክሪን እና የማስታወቂያ ህትመት ማኅበር
  10. አነስተኛ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች አምራቾች ማኅበር
  11. የሹራብ አምራቾች ማኅበር
  12. የሽመና ውጤቶች እና የሥጋጃ አምራቾች ማኅበር
  13. የእንጨት እና የቀርቀሃ ውጤቶች አምራቾች ማኅበር