አባልነት


አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚከተለው መንገድ አባል መሆን ይችላሉ

  1. የንግድ ፈቃዳቸውን እና የግብር መክፈያ ቁጥራቸውን በመያዝ እዚህ ገዕ ላይ ያለውን ኦንላይን ቅጽ በመሙላት ወይንም በአካል ቢሮ በመቅረብ ማመልከት
  2. ማመልከቻው ተቀባይነት ሲያገኝ የአባልነት ክፍያ በመክፈል
  3. የአባልነት መታወቂያ በመውሰድ

የማህበሩ አባላት የሚያገኟቸው ጥቅሞች

  • የስልጠና እና የምክር አገልግሎት
  • የሀገር ውስጥና የውጪ ኤክስፖ መሳተፍ
  • የመረጃ አገልግሎት
  • የተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶች
  • በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል በሚደረግ ውይይት መሳተፍ
  • ችግር ሲገጥማቸው በክ/ከተማው የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ወይም አዲስ አበባ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መተው በማመልከት ምክር ቤቱ የኢንዱስትሪዎችን ችግር ከሚመለከተው ባለድርሻ ጋር እንዲዎያዩና ችግሩ እንዲፈታ ሁኔታዎችን ያመቻቻል

የማህበሩ አባላት የአባልነት ግዴታ


  • የአባልነት ክፍያ በመክፈል የአባልነት የታደሰ መታወቂያ ይዞ መገኘት
  • በተለያዩ የውይይት መደረኮች እና ጠቅላላ ጉባዔዎች ላይ መሳተፍ

የማህበሩ አባላት መብት


  • ኢንዱስትሪው ችግር ሲደርስበት ም/ቤቱ ጥያቄውን እንዲያቀርብለት የመጠየቅ
  • የተለያዩ ስልጠናዎችን የማግኘት መብት
  • የሀገር ውስጥና የውጪ ኤክስፖ የመሳተፍ
  • መረጃዎችን የማግኘት
  • የመምረጥና የመመረጥ መብት
  • ከግብርና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት ጥያቄና ማብራሪያ የመጠየቅ

አባላት ከማህበራችን ጋር በትብብር ሊፈቱ የሚገባቸው ችግሮች ሲያጋጥሙ ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ችግሮቻቸውን በቅጽ ላይ በመሙላት ለማህበሩ ማሳወቅ ይችላሉ